ርዕሠ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የሸኮ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ቲካሸ ቤንጊ ” እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አንዱ የሆነው የሸኮ ብሔር የራሱን የዘመን አቆጣጠር ስልት ጠብቆ ሁነቱን ከሚያከብሩት ብሄረሰቦች ውስጥ አንዱ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል ፡፡

በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ብሔር ዘንድ የሚከበረው ‹‹ ቲካሽ ቤንጊ›› በአካባቢው የምርት መሰብሰቢያ ወቅት መሰረት በማድረግ፣ የግራዋ ዛፍ ሲያብብ ማር የሚቆረጥበት፣ የተጣላን በማስታረቅ፣ ከተገኘው ምርት በአንድ ላይ ማዕድ በመቁረስ ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው ብለዋል።

ቲኬሻ ቤንጊ ቀጣዩ ምርት የተሻለ እንዲሆን እና መጪው ጊዜ ብሩህ እንዲሆን ፈጣሪ የሚለመንበት በዓል መሆኑንም በመልዕክታቸው ገልጸዋል ።

በዓሉ የሸኮ ብሄረሰብ አኗኗርና ባህል የሚገለፅበት ትውልዱ የሸኮን ባህልና አኗኗር እንዲገነዘብ ዕድል የሚሰጥ ባህሉ ይበልጥ እንዲለማና ለቱሪዝም መስህብነት እንዲሆን ከማድረግ አኳያ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ ‹‹ ቲኬሻ ቤንጊ ›› መከበር አብሮነትን፣ ወንድማማመችነትን/ እህትማማችነትን፣ መተሳሰብን፣ሰላምን፣ አርቆ አሳቢነትንና ለባህል ልማትና ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ እጅግ የላቀ በመሆኑ በመጠበቅና በመንከባከብ ትውልድ ተሸጋሪ እንዲሆን የክልሉ መንግስት ትኩረት አድርጎ ያለማል ብለዋል ፡፡

በድጋሚ እንኳን ለሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ ‹‹ ቲኬሻ ቤንጊ ›› በሰላም አደረሳችሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *