በክልሉ የተጀማመሩ ኢንሼቲቮችን በቁርጠኝነት በመምራት የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በተግባር ማረጋገጥ ይገባል።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፤ የአስፈጻሚ ተቋማት እና የፓርቲ የተግባር አፈጻጸም ተገምግሟል።

በክልሉ ለተጀማመሩ ነባር ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት እና እንዲጠናቀቅ በማድረግ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ የገለጹት።

የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና ዘርፎች በክልሉ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተገኘውን ውጤት አጠናሮ ማስቀጠልና በውስንነት የታዩ አፈጻጸሞችን ፈጥኖ ማሻሻል እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።

በክልሉ አንዳንድ ተቋማት የተጀማመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ አዳዲስ በመጀመር ተጨማሪ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየተነሳ መሆኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ የቆሙትን ፕሮጀክቶች ፈጥኖ ማስቀጠል እና ለነባር ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት ማጠናቀቅ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

ለወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ልሰጥ እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች ለዚህ ዓለማ የመደቡትን ሀብት በተገቢው በማውረድ ለተግባሩ ውጤታማነት የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።

በክልሉ የተጀማመሩ ኢንሼትቮችን በቁርጠኝነት በመፈጸም የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በተግባር ማረጋገጥ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ፓርቲ በየጊዜው የአመራር ውጤታማነትና የተግባር አፈጻጸም በመገምገመ አቅጣጫዎች ከማስቀመጥ አኳያ የጀመረው ተግባር አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል።

ፓርቲው በከተሞች ከልማትና ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዘው በህብረተሰቡ

የሚነሱ አዝማሚያዎችን በትኩረት በመገምገም በመፍተሔ አቅጣጫዎች ላይ ከመንግሥት ጋር በቅርበት መስራት ይገባል ያሉት ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በዚህም ረገድ ቅንጅታዊ አሰራሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የኑሮ ውድነት ለመቋቋም በከተሞች የተጀመረው የሰንበት ገበያ ማስፋት እንዲሁም ሰው ሰራሽ የነዳጅ አቅርቦትን በተገቢው መምራት እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያስገነዘቡት።

በአመራር እና አባላት ውስጥ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ራዕይ በተግባር ማሳካት እንደሚገባ የገለጹት የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ በየደረጃው ባለው መዋቅር ተግባራትን በቅንጅት በመምራት የዜጎችን ሁለንተናዊ የብልጽግናና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

”ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መግንሥት ግንባታ የጎላ ሚና አለው” ያሉት አቶ በላይ አደረጃጀቶችን የማጠናከር እንዲሁ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብርና ጤናማ ፉክክር መንፈስ አብሮ የመስራት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት ያልተከናወኑ በተግባራትን ለይቶ መፈጸም እንደሚገባ አንስተዋል።

የክልሉ አጠቃላይ የሶሺዮ ኦኮኖሚ መረጃ እንደሚሰበሰብ፣ክልላዊ አጠቃለይ የምርት መጠን መረጃ እንደሚሰራ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በኢኮኖሚ ፣ በመሰረተ ልማት፣ በማህበራዊ፣ በአስተዳድር እና ህግ ጉዳዮች ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች የተጠቃለለ የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በቀረበው የተጠቃለለ የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ሪፖርት ላይ አስተያየት የሰጡት የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ የህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ አመለካከትና ተግባር መከላከል እንደሚገባ አንስተዋል።

በማዳያ የቀረበውን ነዳጅ ከማስተዳደር አኳያ ያለውን ክፍተት ተከታትለው ማረምና ህግን በተገቢው ማስከበር እንደሚገባ የተናገሩት ተሳታፊዎቹ ተግባራትን በውጤታማነት መምራት ይገባል ነው ያሉት።

የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ፣ስራ ዕድል ፈጠራ በልዩ ትኩረት እንዲመራ፣የቴክንክ ሙያ ተቋማት የተማሪ ቅበላ ማነስ እንዲስተካከል ፣ የኢንቨስትመንት ፖቴንሻል በአግባቡ እንዲለይ፣ ምርትና ገበያን የማስተሳሰር ሥራ ትኩረት እንዲያገኝ፣የማዕድን ስራዎች ዉጤታማነት በደንብ እንዲገመገምና የክልሉ አጠቃላይ የምርት መጠን እንዲሰራ ከተሳታፊዎች አሰተያየት ቀርቧል።

በበጀት ዓመቱ በቀሪ ጊዜያት ያልተሳኩ ተግባራት በልዩ ትኩረት በማጠናቀቅ አፈጻጸሙን ለማሻሻልና የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የገለጹት።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *