ከተሞች ለነዋሪዎች የተመቹ እንዲሆኑ የተጀመሩ ጥረቶች ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን የደካ እና ጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ገለጹ

Spread the love

ደካ እና ጀሙ ከተማ አስተዳደሮች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት በካፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ከሚገኙ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

ሁለቱ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በ2013 ዓ.ም በፈርጅ ሶስት የታቀፉ ከተሞች ሲሆኑ እነዚህን ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

የደካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በላይ ባደገ እንደገለጹት፤ ደካ ከተማን ለነዋሪዎች ለመኖሪያ የተመቸ ለማድረግ አስፈላጊ የመሠረተ ልማት ከመዘርጋት ባሻገር በኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭ ከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት እየሰራ ይገኛል።

በከተማው የመብራት ዝርጋታ ፣የከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታና ጠጠር ማልበስ፣የቦይ-ዲች እንዲሁም የድልድይ ግንባታ ሥራዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን የከተማው የውስጥ ገቢ አቅም ለማሳደግ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም በትኩረት እየተሰራ እንዳለም የከተማ ከንቲባው አንስተዋል።

በግብርናው ዘርፍ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በስራ ዕድል ፈጠራ አኳያም የተለያዩ የብድር አማራጮችን በማፈላለግ በማህበር ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች ድጋፎች መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በከተማው በኮሪደር ልማት የእግረኛ መንገድ፣ የመንገድ ዳር ፖሊ እና መዝናኛ ሥፍራዎች እየተሰራ መሆኑንም ገልጸው ሳይፈቀድ የተያዙ የከተማ መሬት ህጋዊ ለማድረግ ሥራዎች በስፋት እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል የደካ ከተማ ከንቲባ አቶ በላይ ባደገ ።

ጀሙ ከተማ በክልሉ ካሉት ከተደራሽ ከተሞች አንዷ ከመሆን ጋር ተያይዞ ለከተማዋ የሚመጥን በርካታ የከተማ መሠረተ ልማት ለማሟላት ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ እንዳሉም የገለጹት የጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ ናቸው።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ እና ከከተማዉ ማህበረሰብ ተሳትፎ 3.2 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የከተማ የመንገድ ዳር የመብራት ዝርጋት፣በ2.7 ሚሊዮን ብር 4ኪ/ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጠጠር ማልበስ እና 11 ኪ/ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ መከናወኑንም የጀሙ ከተማ ከንቲባ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ከመሠረተ ልማት ሥራዎች ባለፈ የከተማዋን ግብርና ለማዘመን እና ምርትናምርታማነት ለማሳደግ በመስኖ የተለያዩ አትክልትና ሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ክልሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሥራዎች እየተሰሩ እንዳለም ጠቁመዋል።

በከተማ ሳይፈቀድ የተያዙ መሬቶችን ህጋዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት የከተማ ከንቲባው የከተማ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የፓትሮል ቅኝት አባላት ምልመላን ጨምሮ ጸጥታ መዋቅርና የከተማ ነዋሪው በመተባበር በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

የጀሙ ከተማ ከንቲባው በማከልም በከተማዉ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች ስላሉ አልም ባለሀብቶች ወደከተማው መተዉ እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በደካ እና በጀሙ ከተሞች የሚስተዋለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዲፈታ ከተማ አስተዳደሩ ከልማት አጋር ድርጅቶች፣ከማህበረሰብ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተመላክቷል።

በፍቅር ከበደ እና በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *