ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ግልፅ መረጃ በፍጥነትና በአስተማማኝ ሁኔታ በመስጠት ቀውስን መቀነስ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የድህረ እውነት ዘመንን በእውነትና በዕውቀት” በሚል መሪ ቃል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፤ ለህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየቀጠለ ይገኛል።

የቀውስ ጊዜ ኮሙኒኬሽን እና የመረጃ ማጣራት ሂደት ላይ የስልጠና ሰነድ በኢዜአ የሚዲያ ክትትልና መረጃ ማጣራት ዳይረክቶረት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ አብዱ አሊ ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል።

ቀውስ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል ያወሱት አቶ አብዱ ሰልጣኞች የቀውስ ጊዜ ተግባቦትን ባህሪይ፣ የቀውሱ ምንጮችን፣ የቀውስ ደረጃዎችንና መፍትሔውን በውል በመረዳትና መረጃዎችን በማጥራት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት መስራት እንደሚገባ አቶ አብዱ ገልጸዋል።

ቀውስ በትብብር እንደማይፈታ ያነሱት አቶ አብዱ ለሚከሰተው ቀውስ መፍትሔ ለመስጠት የቀውስ ጊዜ ኮሙኒኬሽን ዕውቀትና ክህሎት በመጨበጥ ሀገርንና ህዝብን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ጉዳዮች በፍጥነትና በአስተማማኝ ተግባቦት ቀውስን ማስተዳደር እንደሚገባ ጨምረው አንስተዋል።

በመሆኑም የተቀናጀና የተናበበ፣ ወቅታዊ ፣ ትክክለኛ እና ግልጽ የሆነ መረጃ በመስጠት ሠላምና መረጋጋትን በማስፈን እና የህዝብና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ኃላፊነት መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በመሆኑም የቀውስ ጊዜ ተግባቦት ዑዴቶችን በመለየት ተገቢ ምላሽ በመስጠት ተቀባይነትና ታአማንነት ለማትረፍ በቀጣይነት መስራት ፋይዳው የላቀ መሆኑ ተገልጿል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *