በክልሉ ከተጀመሩ ኢኒሼቲቮች አንዱ የሆነው የሻይ ተክል ልማት ስራን ዉጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ ፡፡

Spread the love

በዘንድሮው የሻይ ተክል ልማት በአዲስ ማሳ 50ሄ/ር ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም ታውቋል ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት በሻይ ተክል ልማት ስራዎች የሚበረታቱ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጿል ፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይ ኮጁዋብ እንደገለጹት የሻይ ተክል ልማት ኢኒሼቲቭ በክልሉ ከተጀመረወዲህ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

በክልሉ በተጀመረው ኢኒሼቲቭ በአዲስ ማሳ 50 ሄክታር ለማልማት ግብ ተይዞ እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ በላይ አስረድተዋል ፡፡

እስካሁን ባለው አፈጻጸም 11.5ሄ/ር የሻይ ተክል የተተከለ ሲሆን ቀሪዉ በቀጣይ የሚተከል ይሆናልሲሉም አቶ በላይ ተናግረዋል ፡፡በቀሪ ወራት በሚተከለው የሻይ ተክል ልማት 25 ሄ/ር በባለሀብት የሚለማ መሆኑንም አቶ በላይ ጨምረው ገልጸዋል ፡፡

የክልሉ መንግስት በራስ አቅም የሚከናወኑ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን ቀርጾ እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በላይ የሻይ ተክል ልማት ስራን በክልሉ በስፋት ለማልማት ልዩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገም ይገኛል ብለዋል ፡፡

በክልሉ ካሉ ዞኖች በካፋ ዞን አራት ወረዳዎች ላይ በ4 ችግኝ ጣቢያዎች እስካሁን 1 ሚሊዮን 22 ሺህ 449 ፖሊ የአፈር ጥቅጣቆ ስራዎች ተከናዉኗል ሲሉም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ፡፡

በተመሳሳይም የሻይ ተክል ልማት ስራን ውጤታማ ለማድረግ በቤንች ሸኮ ዞን በሁለት ወረዳዎች 2 የችግኝ ጣቢያዎችን በመለየት የአፈር ሥራ መጀመሩንም አቶ በላይ አስረድተዋል ፡፡

በክልሉ በሚገኙ ትላልቅ የሻይ ተክል ልማት ድርጅቶች 4 ሺህ 877.3 ቶን የሻይ ልማት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡንም አቶ በላይ አስረድተዋል ፡፡

በዚህም ከካፋ ዞን 3 ሺህ 464.3 ቶንና ከሸካ ዞን 1 ሺህ 413 ቶን የሻይ ልማት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡንና ይህም ዕቅዱን 67.5 በመቶ ማከናወን መቻሉን አቶ በላይ ገልጸዋል ፡፡

ከተገኘው ምርት በኤክስፖርት ደረጃ 899 ቶን ሻይ ልማት ወደ ውጭ ሀገር መላኩንም አቶ በላይ አስረድተዋል ፡፡

እስካሁን በተደረሰበት በልማት ድርጅቶች 1800 ሄ/ር እና በአዉትግሮወር ስኪም በአርሶ አደር 463 ሄ/ር መሆኑም ተጠቅሷል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *