


በምዕራብ ኦሞ ዞን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል
በዓሉ”ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከበረው ፡፡
ለ18ኛ ግዜ የተከበረው ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን ላይ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የምዕራብ አሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት ሠንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያዊያን የአይበገሬነት ምልክት የሀገራችን የኩራት አርማ ነው ብለዋል።
ዘንድሮ የሚከበረው የሠንደቅ ዓላማ ቀን ልዩ የሚያደረገው ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገንብታ በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመንና የማንሰራራት ብሥራት ላይ በመሆናችን የተከበረ ዕለት በመሆኑ ቀኑን ልዩ ያደረጋል ብለዋል።
የዞኑ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ብልልኝ ወ/ሰንበት እንደገለፁት ሠንደቅዓለማ ህዝቦች ለሀገራቸው ያለውን ፍቅርና አንድነት ዳግም የሚያድሱበት ቀን እንደሆነ ተናግረዋል ።
ሠንደቅዓላማ የሀገራችን ብሔራዊ መታወቅያ የህዝቦች ኩራት መሆኑን አቶ ብልልኝ ወ/ስንበት መግለፃቸውን የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል
የጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እንደተናገሩት ሠንደቅዓላማ የሀገራችን ህዝቦች በአንድነት የቆሙለት በመሆኑ የአሁኑ ወጣት ይንን ይዞ መቀጠል አለበት ብለዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
