የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህዝበ ውሳኔ ራሳቸውን ሪፎርም ካደረጉ የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው

Spread the love

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህዝበ ውሳኔ የምርጫ ስርዓት ራሳቸውን መልሰው ሪፎርም ካደረጉ የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።

በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዘህራን ሁመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ጌታ ቸሩ፣ የአራቱ ክልሎች ምክር ቤትና ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እንዲሁም የፀጥታ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በአዲስ የተደራጁ ክልሎች ውሰጥ በሚኖሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል ጠንካራ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማጎልበት የውይይቱ ዓላማ ነው ተብሏል።

በተጎራባች ክልሎች መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በሕዝቦች ተሳትፎ በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ለማስቻል ያለመ ስለመሆኑም ተገልጿል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *