የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት አባላት በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮርደር ልማት እና የመሰቦ አንድ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

የልማት ፕሮጀክቶችን በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ፤ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

እንደ አባላቱ ገለጻ፣ መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው የዴሞክራሲ ስርዓቱን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

የከተማው የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የከተማዋን ገጽታ ስር-ነቀል በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚያስችሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተለያዩ ምዕራፎች ከፍሎ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እያከናወነ መኾኑን ነው የከተማዋ ከንቲባ ተክለአብ ቡሎ (ዶ/ር) እንደገለጹት።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ስኬታማ እንዲኾኑ የኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ሲኾን፣ ይህም የከተማዋን የንግድ፣ የቱሪዝም እና የማኅበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ታላቅ ተስፋ ሰንቋል ብሏል ዶ/ር ተክለአብ።

ከእነዚህ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መካከል ግንባታው ተጠናቆ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት የሚኾነው የቦንጋ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት (One-Stop Center) ዋነኛው መኾኑን የገለጹት ካንቲባው፣

ማዕከሉ ወደ ሥራ ሲገባ 28 ዓይነት የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከልና በተሳለጠ መልኩ በመስጠት የአገልግሎት አሰጣጥ ቢሮክራሲን፣ የነዋሪዎችን እንግልትና አላስፈላጊ ወጪን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የሕዝብን ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *