የጥምቀት በዓል በሸካ ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በቅዳሴ፣ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና በሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ትላንት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ባደሩበት የባህረ ጥምቀት ሥፍራው ከሌሊቱ ጀምሮ ሥርዓተ ቅዳሴና ልዩ ልዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከናወኑ ያደረ ሲሆን በጠዋቱ ክፍለጊዜም የጥምቀት ስነስርዓት በካህናቱ አማካይነት ተከናውኗል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች መከበሩን ቀጥሏል።
በሸካ ዞን 86 ታቦታት የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ጥር 11 ወደ ማደሪያቸው የሚመለሱ ታቦታት ብዛት 61፤በጥር 12 ቀን ደግሞ 23 ታቦታት፤ጥር 13 ቀን 2 ታቦታት ይገባሉ፡፡




