በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል

Spread the love

በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል

በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የተመዘገቡና እጩ ያስመዘገቡ የፖለቲካ ፖርቲዎች እንዲሁም የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው የግል ተወዳዳሪዎች ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳና የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ እንደሚችሉ ቦርዱ አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ እና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተካሄደ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፍ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር)፣ የክልሎች አፈ ጉባኤዎችና ምክትል አፈ ጉባኤዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ “የሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝግጅትና የምክር ቤቶች ሚና” በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።

ምክትል ሰብሳቢው በገለፃቸው፤ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ እንዲከናወን እና የድምፅ መስጫው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሆን ቦርዱ መወሰኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይሄንን ታሳቢ በማድረግ የግብዓት ማሟላት፣ የስልጠናና ግንዛቤ የመፍጠሪያ የተለያዩ ዝግጅቶችን ማድረጉን ገልጸዋል።

በዚህም ቦርዱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከመደበኛ የምርጫ ጣቢያዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በሥራ ምክንያት በተለያየ ቦታ የሚገኙ ዜጎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዋት አባላት እና ሌሎች ልዩ የምርጫ ጣቢያ ሊቋቋምላቸው የሚገባ ስለሆነ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራታቸውን ገልጸዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩ የገለጹት ምክትል ሰብሳቢው፤ በአዋጁ መሰረት እያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ ከ 1 ሺህ 500 የማይበልጥ መራጭ መያዝ አለበት ብለዋል።

በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የምርጫ ስራዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለቦርዱ አቅም የሚፈጥሩ ድንጋጌዎች መካተታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ እንዲሁም ሌሎች የቦርዱን ስራ ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉና የቅሬታ አፈታት ስልቶች ማሻሻያ እንደተደረገባቸው ጠቅሰዋል።

በአጠቃለይ ቦርዱ በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ ምርጫውን ማከናወን የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

መራጮች በዲጂታል ወይም በአካል በመቅረብ መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መተግበሪያ አማካኝነት ባሉበት ሆነው መመዝገብ የሚፈልጉ መራጮች የብሔራዊ መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቦርዱ የተመለመሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ከማንኛውም የፖለተካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆኑ ለስራው በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውና የአካባቢውን የስራ ቋንቋና ባህል የሚያውቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመላ ሀገሪቱ ቢያንስ 318 ሺህ ምርጫ አስፈፃሚ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡

የፖለቲካ ፖርቲዎች የፅሁፍና የቃል ፈተናውን ያለፉ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ገለልተኝነት በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጓል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.social

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *