በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፋት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል፦ አፈጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ

Spread the love

በክልሉ ምክር ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 7ኛ ዙር ፎረም ላይ የተሳተፉ የክልልና የዞን አመራሮች ልዑክ በሚዛን አማን ከተማ አማን ቀበሌ የመስክ ጉብኝት አካሂዷል።

በመስክ ምልከታው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ የክልሉ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶጌታቸው ኬኒን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ምክር አባላቶች ተሳታፊዎች ሆነዋል።

አፈጉባኤዎቹ ጉብኝታቸው በአማን ቀበሌ እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል ።

ከጉብኝት በሻገር የ2018 ዓ.ም የቀበሌ እቅድ አፈጻጸም ቀርበው ዉይይት እና አስተያየት ተሰጥቶታል።

የክልሉ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩሩታ እንደተናገሩት በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን በአማን መቀበሌ ጉብኝት የተደረገው የሌማት ትሩፋትና ሌሎች የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አንስተዋል።

በቀበሌው ዛሬ ምልከታ የተደረገው የተለያዩ የልማት ሥራዎች ልምድ የሚወሰድበትና ተሞክሮ ከመሆኑም ባሻገር መንግሥት በየጊዜው የሚያወርዳቸው ኢንሼቮች የምክር ቤት አባላት ተግባራዊ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ እንዳለ አይነተኛ ማሣያ መሆኑን አክለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፋት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል።

የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጌታቸው ኬኒ በበኩላቸው የክልሉን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ምክርቤት አደረጃጀቶችን ማጠናከር፣ አፈጻጸማቸውን መከታተልና መልካም ተሞክሮዎችን የሚወስዱት የጋራ ቅንጂታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ዋና አፈጉባኤ አቶ ጌድዮን ኮስታብ ከመስክ ጉብኝት የተሰጡ መልካም አፈጻጸም የበለጠ በማጠናከርና በጉድለት የተገመገሙትን ተፈጥሮ በማረም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከታችኛው ምክር ቤቶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

የፎረሙ ተሳታፊ የምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችም ተሞክሮውን ወደ መጡበት አካባቢ በመወሰድ በማስፋት የሕዝብ ተጠቃሚነት ላይ አተኩረው እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *