የኢትዮጵያን የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በጥራትና ፍጥነት ለመገንባት በቁርጠኝነት ይሰራል – አሊኮ ዳንጎቴ

Spread the love

የኢትዮጵያን የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በጥራትና ፍጥነት ለመገንባት በቁርጠኝነት ይሰራል – አሊኮ ዳንጎቴ

በዓመት እስከ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርተውን ፋብሪካ በጥራትና ፍጥነት ለመገንባት በቁርጠኝነት ይሰራል አሉ የዳንጎቴ ግሩፕ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎ አሊኮ ዳንጎቴ እንዳሉት ÷ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ማዳበሪያ ከውጭ ታስገባ ለነበረችው ኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥና መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ ዘርፎች ጥሩ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቁመው ÷ በተለይም በሀገሪቱ በቂና ዘርፈ ብዙ የግብዓት አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

ግዙፉ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ እንደሚያደርጋት አስረድተዋል፡፡

በዓመት እስከ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርተውን ፋብሪካ ÷በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

የማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለውን ውጤት ይበልጥ እንደሚያጠናክር አስረድተዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኘው፤ እኔ የውጭ ሀገር ሰው አይደለሁም፣ አፍሪካዊ ነኝ፤ ስለሆነም ለኢትዮጵያ እድገት የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ ነኝ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ባለራዕዩ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዘርፉ እያከናወኑት የሚገኙት ዘመኑን የዋጀ ሥራ የሚደነቅ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በማስፋፋት የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የኢትዮጵያ ብልፅግናን እውን ለማድረግ አበረታች ሥራ እየሰሩ እንደሚገኙም አውስተዋል፡፡

2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካው በ40 ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *