




በሸኮ ከተማ አስተዳደር”የጉባ ብስራቶች የመደመር ትሩፋቶች”በሚል ህዝባዊ ውይይት አየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ በንግግራቸው እንደገለፁት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በሀገራችን በርካታ ተግባራት ከማከናወንም ባለፈ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ክፍተቶን በማረም የሀገሪቱን ልማት የሚያስቀጥል ፓረቲ ነው ብለዋል ገልፀዋል።
ፓረቲው ህዝቡ የራሱ አሻራ በሆነው በጋራ እንዲወያይ ካደረገው ውስጥ የህዳሴ ግድብ አንዱ መሆኑንና ህዳሴ ግድብ የነበረበትን የፋይናንስና የኢኮኖሚ ችግር በመፍታት ዛሬ ለምረቃ መብቃቱ በአለም ደረጃ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስም አስሰጥቷል ብለዋል ኃላፊው።
ሀገራችን ጉልበት፣ ገንዘብና ውሃ ይዛ ለምን አልተቀየረችም በሚል በረካታና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ቀረፃ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ላይ እየሰራች እንደሚገኝ አቶ ተመስገን ተናገረዋል።
ሌብነት ፣ሙስና፣ ደህንነትና የኃላ ቀር ችግሮችን ሀገራችን መንጥቃ በማውጣት በረካታ ውጤቶች እንዲመዘገብ በማደረግ የራሷን ከፍታ እያሰመዘገበች እንደሚገኝ ኃላፊው አብራርተዋል።
የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከዓመት ከ4 ወር ዕድሜ ውስጥ በረካታ ለውጦችን ማስመዘገቧን የገለፁት አቶ ተመስገን ቀሪ ሥራዎችን ህዝቡ ከከተማ መንግስት ጋር በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዘበዋል።
ኢትዮጵያ ጀምራ አትጨርስም የተባለውን የህዳሴ ግድብን በልጆቿ እልህ አስጨራጭ ጥረት በማጠናቀቅ ለሌሎች ሀገራትም ኢትዮጵ ተምሳሌት መሆን መቻሏን አቶ ታምራት ምናሴ የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አንስተዋል።
የራስን ችግር በራስ መፍታት የሚያስችልም በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ያለ መንግስትና ገዢው ፓረቲ እንደሆነም ከንቲባው ተናግረዋል።
ከከተማው ህዝብ ጋር የሚደረጉ የውይይት መድረኮች ክፍተቶችን በጋራ ለይቶ ለመስራትና የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን አቶ ታምራት አክለው ገልፀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስተው በልማትና መልካም አስተዳደር ዘርፍ በረካታ ለውጥ መመዘገቡን በንግግራቸው ገልፀዋል።
በተለይም የከተማውን ህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥና ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።
የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል ከዚህ ውይይት በኃላ የተሻለ ተግባራት እንደሚከናው አቶ ታምራት ገልፀዋል።
በሸኮ ከተማ አስተዳደር”የጉባ ብስራቶች የመደመር ትሩፋቶች”በሚል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።
