ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የሴቶች ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ።

Spread the love

የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች “ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የሴቶች ሚና” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዋጋዬ ዋጄ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤን ሴቶች ለማፅናት የተለያዩ አደረጃጀቶች በማጠናከር መንቀሳቀስና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ፓርቲው እሳቤውን በአባሉ ላይ በመዝራት ፍርያማና ተጨባጭ ውጤቶችን እያሳዬ የሚገኝ እንደሆነ አስረድተዋል።

ኃላፊዋ ባቀረቡት ሰነድ ሴቶች ለሀገሪቱ ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ጉልህ ሚና ያላቸው ስለመሆኑ ገልፀው ይህንንም በየአደረጃጀቶችና በየማህበራዊ መሠረቶች በመወያየትና ግንዛቤ በመፍጠር የበለጠ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በሀገሪቱ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የሴቶች ሚና የጎላ እንደሆነ አንስተው በተለይም በሰላም እጦት ተጎጂዎች ሴቶች በመሆናቸው ለሰላም ግንባታ እና ለገዥ ትርክት መፅናት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች መሠል መድረኮች መፈጠር ሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ አቅም እንደሚሆን አመላክተዋል።

በመድረኩ የጥያቄና መልስ ውድድርና የተለያዩ ስነ ጽሁፍ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን የተሻለ ውጤት ላመጡ አካላት ሽልማት ተበርክቷል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *