ከሪበላ ሐይቅ:-ዉብ ተፈጥሮ ማራኪ መዝናኛ

Spread the love

የለውጡ መንግስት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ሲሆን ያንኑ እኒሼቲቭ እያስፋፉ ካሉት አካባቢዎች አንዱ ኮንታ ዞን ነው።

በዞኑ ተዝቆ የማያልቁ የቱሪዝም ሀብቶች መካከል አንዱ በኤላ ሃንቻኖ ወረዳ ከሪበላ ባደጉቻ ቀበሌ የሚገኘው ከሪበላ ሐይቅ ነው።

ሐይቁ ውብ ቀለም በሚሰጡ ተፈጥሯዊ ጥቅጥቅ ደኖችና ዘንባባ ቀለማት የተሞሸረ በመሆኑ ለአይን ተጨማሪ እፎይታ ይሰጣል።

ይህ ውብ ስራ ተፈጥሯዊ ይዞታን ሳይለቅ ለምተው ለጎብኝዎችና ፊልም አገልግሎት እንዲውል አርቲስት ወንድዬ አበበ (ወንደ ኮንታ) ከዞኑ ጋር በመተባበር “ቶካ የፊልም መንደርና ኢኮ ቱሪዝም” ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተዋወቅ እንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ተመልክተናል።

በውስጡ የመዝናኛውን ዓለም ከሚያስተጋቡ ጉማሬዎች በተጨማሪ በፕሮጀክቱ አማካኝነት የተለያዩ የዓሳ ዝሪያዎች እየተለማመዱ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ሠራተኞች ተናግረዋል።

በመልማት ላይ ያለው ይህ መንደር ለብዙ ወጣት የጥበብ ሰዎች አቅም የሚሆንና በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በሀገር ደረጃ ልዩነትን የሚፈጥር የጥበብና የመዝናኛ ስፍራ እንደሚሆን የፕሮጀክቱ ምክትል ስራአስኪያዥ ወንድይፍራው ማለሎ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ የሐይቁን ዙሪያ ማልማት ሲጀምር ለ 70 ሰዎች ጊዜያዊ ስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 10 ቋሚ ሰራተኞችን ይዘው አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ምክትል ስራአስኪያጁ ገልጸዋል።

ከቀን ሠራተኝነት እስከ ቋሚ ሠራተኝነት የተሸጋገሩ ወጣቶች በዚሁ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በጸጥታው፣ በቅዘፋና በማስጎብኘት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የዕድሉ ተጠቃሚ ሠራተኞች ተናግረዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *