ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አካሄዱ

Spread the love

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትን እና ትስስርን ለማጠናከር ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያን ባህሎችና ዕሴቶችን በማወቅ አብሮነትና ትስስርን ለማጠናከር እንደሚያስችል ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተናግረዋል።

በጎነት ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ለበርካታ ወገኖች ለመድረስ ጉልህ ሚና አለውም ብለዋል።

በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ ሀገራቸውን አውቀው ለሌሎችም እንዲያሳውቁ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ችግኝ በመትከል ለቀጣዩ ትውልድ የለመለመች ሀገርን ለማስረከብ የጀመርነውን ስራ ዘላቂ እንዲሆን እንሰራለን ያሉት ተሳታፊዎቹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህሊና እርካታ የሚሰጥ ሰብዓዊ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ ያካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደሀገር ለመተግበር የተያዘው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀግብር ለማሳካት እና ፅዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንደሆነም ተናግረዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን በዘገባው አመላክቷል።

ከተለያዩ የሀገርቱ ክፍል የተውጣጡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባከናወኑት የችግኝ ተከላ እና የፅዳት ዘመቻ ተግባር ላይ የክልል፣የሸካ ዞንና የቴፒ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *