የቴፒ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያና የቡና ቅምሻ ማዕከል ተመረቅዉ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

Spread the love

የተመረቁት ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፋይዳው የላቀ መሆኑም ተጠቁሟል።

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በምረቃዉ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገኘ ነው ብለዋል።

በዞኑ ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ ቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመም ሰብሎች በስፋት የሚመረት ሲሆን የቡና ጥራት ሰርተፊኬሽን ማዕከሉ መመረቅ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ ያሳልጣል ብለዋል።

የቴፒ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩ ለኢትዮጵያ የመንሰራራትና የከፍታ ምሳሌ ነውም ብለዋል።

ብልጽግና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ይህንን ውጤታማ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።

በክልሉ በቦንጋ፣በሚዛን አማንና በቴፒ ከተማ የተጀመሩት የአውሮፕላን ማረፊያ ልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ስራ እንዲገቡ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።

በታርጫና በማጂ ቱም ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ለዘመናት በመቋረጣቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ ያደርግ ዘንድ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸውም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።

በሀገራችን የአነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ልማት ፕሮጀክቶች መኖር ለሜጋ ፕሮጀክቶች ተደራሽነት፣ለማዕድን ልማት ስራዎችና ለቱሪዝም ና መዝናኛ እንዲሁምለሰብዓዊ አገልግሎት ያላቸው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል ።

እንደ ሀገር የአነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ልማት ጥያቄዎች ከቀረቡት ውስጥ አንዱ የቴፒ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲሆን መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ ምላሽ መስጠቱንም ተናግረዋል ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ በይፋ ስራ የጀመረውን የቴፒ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል።

በክልሉ መሰል ጥያቄዎችንም ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲሰጣቸውም ይደረጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በሰኔ ወር ብቻ 59 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 409 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

እንደ ሀገር በዓመት 468 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱም አቶ ሻፊ ተናግረዋል ።

የቴፒ ቡና ምርት ጥራት ምርመራና ሰርተፊኬሽን ማዕከል ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ማደግ ሚናው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ዛሬ የተመረቀውን የቡና ጥራት ምርመራና ሰርተፊኬሽን ማዕከል ጨምሮ በሀገሪቱ ወደ 7 ደርሷል ያሉት አቶ ሻፊ በቀጣይም 6 የቡና ቅምሻ ማዕከላትን በማቋቋም ወደ 13 እናደርሳለን ብለዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ባስተላለፉት መልዕክት ዞኑ ዕምቅ የተፈጥሮ የደን ሽፋን ያለበትና ለቡናና ሻይ ልማት ስራዎች ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል።

መንግስት የየብስና የምድር ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ በአካባቢው ያለውን ብዝሃ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ተሻለ የገበያ አማራጭ በማቅረብ ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

87 ሺህ ሄክታር የሚሆን ቡና በዞኑ አንደሚገኝም አቶ አበበ ተናግረዋል ። 17 ሺህ ሄክታር በቅመማ ቅመም ሰብሎች እየለማ ይገኛልም ብለዋል ።

የኢትዮጵያ ሲቪላይዜሽን ባለስልጣን ሳይቋረጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ አቶ አበበ ጠይቀዋል ።

በዕለቱም የፌደራል፣የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *