በሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በብሪክስ የስፖርት ዘርፍ መድረክ እየተሳተፈ ነው

Spread the love

በፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በብሪክስ የስፖርት ዘርፍ መድረክ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የብሪክስ አባል ሀገራት የስፖርት ዘርፍ መድረክ በስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመከላከል ዙሪያ የሚመክር መድረክ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመድረኩም የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶን (ዶ/ር) ጨምሮ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በነገው እለት የሚጠናቀቀው መድረኩ በኦስትሪያ ቬይና እየተካሄደ እንደሚገኝ ከፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *