




አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የደረሰው ኦሞ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 213 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል።
ባንኩ ይህንን ያስታወቀው 4ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ነው።
የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል።
ልማት ተኮር ራዕዩን ለማሳካት በግብር እና ንግድ እንዲሁም በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ዘርፍ ለተሰማሩ 91 ሺህ ደንበኞቹ 3 ቢሊዮን 565 ሚሊዮን 175 ሺህ 710 ብር ብድር ማሰራጨቱን ባንኩ ገልጿል።
በአዲስ አበባ እና በአራት ክልሎች ውስጥ የቅርንጫፍ ብዛቱን 241 ማድረሱን እና የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም 6.4 ቢሊዮን ብር መሻገሩንም ነው ያስታወቀው ኢቢሲ ዘግቧል።
በተያዘው 2018 በጀት ዓመትም የውስጥ አሠራሩን በማጠናከር ካፒታሉን ለማሳደግ ማለሙን እና የዲጂታል ፋይናንስን ላይ አጠናክሮ እንደሚሠራ ይፋ አድርጓል።
