የ‎ክልሉ ድጋፍ ቡድን በሸካ ዞን ማሻ ከተማ የተለያዩ የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን ምልከታ አደረጉ

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ በሆኑት በአቶ በላይ ተሰማ የተመራው የክልሉ የድጋፍ ቡድን ማሻ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

‎የድጋፍ ቡድኑ በማሻ ከተማ በመንግስትና በፓርቲ መሪነት በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት፣ የፓርቲ አደረጃጀት ቁመና ምልከታ አድርገዋል።

‎በመስክ ምልከታው በሌማት ትሩፋት በከተማ ግብርና እየተከናወኑ ያሉ አሳ እርባታ ፣ የዶሮ እርባታ ጨምሮ የንብ ማነብ ስራዎችና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተጓብኝተዋል።

‎የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ የድጋፍና ክትትል ዓላማው በበጀት ዓመቱ በፓርቲ ክንፍ የታቀዱ ተግባራትና አፈፃፀማቸው መከታተል በፓርቲ መሪነት የመጡ ውጤቶችን መቀመርና ተሞክሮ ማስፋፋት ጨምሮ የማህበረሰቡ የኑሮ ዋስትና ሊያረጋጥ በሚችልብ መልኩ የከተማ ግብርናን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በከተማው የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ይህንን አጠናክሮ በማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

‎በማሻ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የአባላትና የአደረጃጀት ዕቅድ የተዘጋጀ መሆኑ፣ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት ጥሩ መሆኑ፣ የአባላት መዋጮ አሰባሰብ የተሻለ መሆኑ ፣ የራሱ የሆነ በፓርቲ መወያያ ቤቶች መኖራቸው ፣ አጠቃላይ በቀበሌው የፓርቲ ስራዎች በተግባር የተረጋገጠበት መሆኑን ሱፐርቪዥን ቡድኑ በጥንካሬ አንስተዋል ።

‎የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው በከተማው የዋጋ ንረት ለመቀነስ የሰንበት ገበያ በማቋቋም የተሻሉ ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆኑን ገልጸው ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በከተማ ግብርና የንብ ማነብ ስራ ላይ ተሰማርተው ውጤታማ ከሆኑት አቶ ክብሮም ከበደ አንዱ ሲሆኑ ስራውን በቅርብ ጊዜ የጀመሩ ቢሆንም የተሻለና ዘመናዊ የአሰራር ስረዓትን በመዘርጋት የተሻለ የምርት አቅርቦት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን በድጋፍና ክትትሉ ለመመልከት ተችሏል።

‎በድጋፍ ቡድኑ ምልከታ ከተደረገባቸው በዶሮ እርባታ ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ ካሉ አቶ ኃይሌ ደንቦ ሸጎ መታሰቢያ የዶሮ እርባታ ማህበር ተጠቃሽ ሲሆን ወደ 8 መቶ የሚሆኑ የተሻሉ የዶሮ ዝርያዎችን በመያዝ ስራ ላይ መሆኑን የተናገሩት የእርባታው ባለቤት አቶ ብርሃኑ ኃይሌ በቀን እስከ 5 መቶ የሚጠጉ እንቁላሎችን ለገበያ ማቅረብ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

‎የዶሮ እርባታ በተሻለ ሁኔታ ለማስኬድና የእንቁላል አቅርቦት መጠን ለመጨመር የከተማ አስተዳደሩ የዶሮ እርባታ ቦታ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

‎የድጋፍ ቡድኑ በቀጣይ በሌሎች ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *