በክልሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር የክልሉ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ።

Spread the love

ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር የተገጠሙ መሆናቸውም ተገልጿል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብዝሃ ማዕከላት አደረጃጀት ተዘርግቶ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል ።

በክልሉ አራት ብዝሃ ከተሞችና ሁለት ተደራሽ ከተሞች ተቋቁመው የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የክልሉ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው እንደገለጹት በክልሉ ሁሉም ከተሞች የተሳለጠ የቪዲዮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የመግጠም ስራ መጠናቀቁን ተናግረዋል ።

የኢፌዲሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ ካሜራዎችን ድጋፍ ማድረጉን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ዜጎች ያለእንግልት ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንዲደራጁ ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል ።

ለቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት የሚውሉ የቴሌቪዥን ስክሪኖችን በመግዛትና በስድስት ከተሞች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የመግጠም ስራዎች ተጠናቀዋል ሲሉም አቶ ተስፋዬ ጨምረው ገልጸዋል።

በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም የቢሮ ኃላፊዉ ገልጸዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *