
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመንግስት ገቢ በእጅጉን ጨምሯል፡፡ ባላፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ እድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ 109 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት አንጻር አሁንም ዝቅተኛ ገቢ የምትሰበስብ ሀገር ናት፡፡ ይህ በቀጣይ መሻሻል አለበት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
