የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመማር ማስተማር ሂደት ተጎበኘ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር እና የተግባር ማሰልጠኛ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

ኮሌጁ ተማሪዎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ክህሎት እንዲጨብጡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል።

ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት የንድፈ-ሀሳብ ትምህርቱን ከተግባር ጋር ማቀናጀቱ ለጤናው ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል።

የመማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ለማዘመን የቤተ-መጻህፍት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረግ አስፈላጊነት ላይ መግባባት መፈጠሩን ከዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ኮሌጁ የክልሉን የጤና ባለሙያ ፍላጎት ለማሟላትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *