የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው የላቀ አበርክቶ አድርገዋል – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

Spread the love

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ ቀኑን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ማህበራዊ እሴቶችና ባህሎችን ለማፅናት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የላቀ ነው ብለዋል።

እንቅፋቶችንና ጎታች እሳቤዎችን በመጣል፣ በመላ አቅማቸው የኢትዮጵያን የመዘመን መንገድ ዋነኛ መሪና ተዋናይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *