የ2017 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ በክልላችን “የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን”በሚል መሪ ቃል በጥር 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል ።አቶ የሺዋስ ዓለሙ

Spread the love

የዘንድሮው 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት የተፈጥሮ ሀብት የመሬት ፣ የውሃና የሰው ሀብታችንን መጠበቅ ፣ ማልማትና በላቀ ደረጃ በማቀናጀት ጥቅም ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የማህበረሰብ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በተመለከተ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ የሺዋስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ2017 የማህበረሰብ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በክልል ደረጃ ጥር 22/2017 ዓ.ም በይፋ የሚጀመር መሆኑን ተናግረዋል ።

“የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነዉ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በዚህ ዓመት በከፍተኛ ህዝብ ንቅናቄ የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

የተፋሰስ ልማት ስራው ለተከታታይ ለ45 ቀናት የሚከናወን መሆኑንም አቶ የሺዋስ ገልጸዋል።

የ2017 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ዉጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ የክልላችን ግብርና ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ክልላዊ የአሰልጠኞች ስልጠና መሰጠቱንም አመላክተዋል።

ለዘንድሮው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ቀያሽ አርሶ አደር ስልጠና መስጠት፣ ንዑስ ተፋሰስ መለየትና ጥናትና ዲዛይን ስራ ፣ ኃይል ልየታ፣ የእጅ መሳሪያ እና የቅየሳ መሳሪያ ልየታ ከወትሮ በተለየ በዚህ ዓመት በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የማህበረሰብ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራዎች ከ2014 ዓ.ም-2016 ዓ.ም ባሉት ዓመታት 1562 ንዑስ ተፋሰስ 453 ሺህ 696 ሄ/ር ማልማት መቻሉንም ጠቅሰዋል ፡፡

የወጣቶችን ስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ በመደበኛ ተፋስስ እና በፕሮግራምና ፕሮጀክት ተፋሰስ 28 ሺህ 773 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።

በ2017 ዓ.ም በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራዎች 225 ሺህ ሄ/ር ንዑስ ተፋሰሶች እንደሚለሙ ጠቅሰዋል።

1 ሚሊዮን 15 ሺህ 312 የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የሚሰራ ይሆናል ሲሉም አቶ የሺዋስ ተናግረዋል ።

በ2017 ዓ.ም. የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ ለ996 ንዑስ ተፋሰስ የጥናትና ዲዛይን ሥራ መዘጋጀቱንም አቶ የሺዋስ አብራርተዋል ፡፡

የክልላችን ህዝብም በዚህ ንቅናቄ ስራ በንቃት እንዲሳተፍ አቶ የሺዋስ ጥሪ አቅርበዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *