
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ለሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ለሆነው “ቲካሻ ቤንጊ” በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ማስረሻ በላቸው በመልዕክታቸው “ቲካሻ ቤንጊ” የሸኮ ሕዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት፣ በብሔረሰቡ አባቶች እውቀት ተመርቶ ዘመኑን የሚሻገርበት እና የለምለም ምድሩን ገፀ በረከት ፈጣሪውን እያመሰገነ የሚቋደስበትም ቀን ነው ብለዋል።
የሸኮ ወንድምና እህት ህዝቦች ከሰውና ተፈጥሮ ጋር ተዋደውና ተስማምቶ የመኖር እሴታቸው ጥብቅ ነው እንደሆነም ገልጸዋል።
በዚህ ክብረ በዓል የሸኮ ህዝቦች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ያላቸው የአንድነት፣የመተሳሰብና የአብሮነት እሴት ይበልጥ ተጠናክሮ የሚታይበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
