

የሸካ ዞን ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያ ፕሮግራም በማሻ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በብልፅግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ ሰው ተኮር ተግባር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መገለጫ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም በትኩረት ልተገብረው ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ወቅት ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በልዩ ዲስፒሊን የዘወትር ተግባሩ አድርጎ ዕለት ተዕለት ልፈፅመው ይገባል በማለት አሳስበዋል አቶ አለማየሁ።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ከበደ በበኩላቸው በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት በ14 ልዩ ልዩ የስምሪት መስኮች ከ75 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።
ለበጎ ፈቃድ ተግባር አገልግሎት ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ተቋማትንና ግለሰቦችን አመስግነዋል ወይዘሮ ትዕግስት።
በፕሮግራሙ ላይ የሸካ ዞን፣የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን የ2016 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ማጠቃለያ ሪፖርት፣የእውቅና አሰጣጥን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዝግጅት የመርሃግብሩ አካል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
