



”የጉባ ብስራቶች፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሕዝብና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በአከባቢው በብዝሀ ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ብልፅግና ለመቀየር የሥራ ባህልን በመቀየር ጠንክሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለተረጂነት የሚመች አካባቢ ያለመሆኑን የገለጹት ዶክተሩ የግብርና ሽግግሩ እንዲረጋገጥ ምርቶችን በብዛትና በጥራት ማምረት ይጠበቃል ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተገነባው ገበታ ለትውልድ የደንቢ ሎጅ የአከባቢው የቱሪዝም እንቅስቃሴ እያነቃቃ በመሆኑ ወደ ከተማ የሚመጡ ቱሪስቶች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ አገልግሎት አሰጣጥ ማቀላጠፍ ይገባልም ብለዋል ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ።
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) እንዳሉት ፤ ከከተማ ማኅበረሰብ በመንግስት በኩል እንዲፈታላቸው የተጠየቁ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ ይሰራል።
በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ በመፍጠር፣ መፍጠንና በመዝለል ይሰራል ያሉት ዶክተር መቅደስ በዚህም የህዝቡን የልማት አቅም በተገቢው መጠቀም ይገባልም ብለዋል።
በከተማው ግልጽነት እና ተጠያቂነት በማስፈን የህዝብን እሮሮ ለመመለስ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲስፋፋ እና እንዲጠናከር መሥራት እንደሚገባ ነው ሚኒስትሯ ያብራሩት።
የባህር በር ጥያቄ ለመመለስ የመደመር መንግስት የጀመረውን ጉዞ እንዲሳካ የማህበረሰቡ ድጋፍና ትብብር እንዲጠናከርም አንስተዋል።
ከማኅበረሰቡ ጤና ተቋማት ደረጃ ማሻሻል፣ ማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት መሻሻል ጋር በተያያዘ ህዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች በተጠናከረ ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራም አንስተዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው በዞኑ የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአከባቢው በብዝሀ ዘርፍ ያለው እምቅ ሀብት ወደ ውጤት
ሚዛን አማን ከተማ ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ የተጀመረው ስማርት ሲቲ ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ሰለሞን ለዊ ተናግረዋል።
በፍቅር ከበደ
