በየተቋማቱ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በተገቢው በማረም የህግ ተከባሪነትን የማረጋገጥ ስራ ትኩረት ይሰጠዋል።(ዶ/ር ኢ/ር) ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ የተለያዩ አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ተጠናቋል።

በመድረኩ የስድስት ዞኖችእና የክልሉ ብልጽግና ማዕከል የኮንፈረንስ የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በቀሩቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከኮንፈረንስ ተሳታፊዎች አስተያየቶች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በየዞኑ የተደረጉት ውይይቶች በተገቢውም ስኬቶቻችንን ያየንበትና ጉድለቶቻችንን የለየንበት ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ ነው ብለዋልተሳታፊዎች።

ተሳታፊዎች በፓርቲው እሳቤዎች የታመነ ቃል የተለወጠ ባህል ልንፈጥርና ልንገነባ ይገባናል ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በምናከናውናቸው ተግባራት ውስጥ ፍጥነትንና ጥራትን በማከል ለለውጥ መጣር ከአባላት የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

ክልላዊ የጸጥታ ስራዎቻችን ላይ የተጠናከረ ህብረብሔራዊነትንና አንድነትን በማጠናከር ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመውጣት ህዝቡን አሻጋሪ የሆኑ ልማቶችን ማረጋገጥ ከአባሉ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት ማብራሪያም የፓርቲውን ተልዕኮ ወስዶ ለመፈጸም የታየው ቁርጠኝነት የተረጋገጠበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ነው ብለዋል።

በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ነጠላ ትርክቶችን በተለይም ከፋፋይና አብሮነትን የሚሸረሽሩ ነጣጣይ አስተሳሰቦችን በመፈተሽ ማረም ይገባል ብለዋል።

ከዚህም አኳያ አብሮነትንና አንድነትን የሚሸረሽሩ ሀሰተኛ ሚዲያዎችን አመራሩና አባሉ የሰላ ትግል በማድረግ ሀሳባቸውንና ተልዕኳቸውን ያለምህረት መታገል ይገባናል ብለዋል።

መድረኩን ያጠቃለሉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በየደረጃው የተከናወነው የአመራርና የአባላት ኮንፈረንሶች ቁርጠኝነት የታከለበት ሊበረታታ የሚገባውና ቀጣይነት ሊኖረው የሚገባ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ባለፉት የለውጥ ጊዜያት በኢኮኖሚው ለውጥ በማምጣት፣ገዢ ትርክትን በመገንባት በማህበራዊ ፣በፖለቲካው ፣በዲፕሎማሲ መንገድ ተጨባጭ ለውጦች ተገኝተዋል ብለዋል።

በክልሉ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያልቁ ስራዎችን በመተግበር ህብረብሔራዊነትን ማጠናከር ይገባናል ብለዋል።

ያለመተማመንና ጥርጣሬን የሚፈጥሩ ሀሳቦችን በመቀራረብ ልናርማቸውም ይገባል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ።

የክልሉን የመልማት እምቅ አቅሞች በመለየት ጸጋዎችን ወደ ለውጥ መቀየር ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራልም ሲሉ ተናግረዋል ።

በየተቋማቱ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በተገቢው በማረም የህግ ተከባሪነትን የማረጋገጥ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠውም ተናግረዋል።

አጠቃላይ አመራሩና አባሉ የተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ አስተያየቶች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት እንዲሁም የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *