




በደብረ ብርሃን ከተማ” የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የተከበሩ ማስረሻ በላቸው፣ና የሸገር ከተማ ከንቲባና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት በ1446 በተጎራቆረችው በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ፣የቱሪዝምና የዕውቀት ከተማ እንድትሆን በሚሰራበት ደጋማ የሸዋ ብርሃን ደብረ ብርሃን እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል።
የውይይቱ ዓላማ የጉባ ብስራቶች እና የመደመር መንግስት ትሩፋቶች ምን እንደሆኑ ለማስገንዘብ፣ ሰላምን በማጽናት ልማትን ለማስቀጠል እና ሕዝብ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያለመ መኾኑን ጠቁመዋል።
በመሆኑም የከተማው ሕዝብ እንደተለመደው ሀሳብ በማንሳት እና በመወያየት በቀጣይ ለሰላም፣ለልማትና ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ የድርሻውን ኃላፊነት እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ማስረሻ በላቸው የመደመር መንግስታችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያሳካቸው በርካታ የልማት ትሩፋቶች መኖራቸውን ዘርዝረዋል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲመረቅ በጉባ ሰማይ ስር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ ያደረጓቸው ይፋ ያደረጓቸው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኒውክለር ሀይል ማብለያ፣የከተማና የገጠር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣የቢሾፍቱ የአየር ማረፊያ የሚጠቀሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በዚህ መድረክ በጉባ ብስራቶች፣በሰላም በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙርያ በጥልቀት ውይይት በማድረግ በቀጣይሰላምን በማጽናት ልማትን ለማረጋገጥ መንግስትና ህዝብ እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ እንደኾነ አመልክተዋል።
ደብረ ብርሃን እንደ ስሟ የብልጽግና ብርሃን እየፈነጠቀባት ያለች ከተማ ነች ብል ማጋነን አይሆንም ያሉት ክቡር ማስረሻ ለዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሃገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ማሳያና ማስወንጨፊያ ማዕከል እየሆነች ነው ብለዋል።
ይህ ውጤት የመጣው አልጋ በአልጋ ሳይሆን በብዙ ተግዳሮት ውስጥ በማለፍ መንግስት ለልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት መሆኑንም አንስተዋል።
በመኾኑም መድረኩ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ስለሆነ ሁላችሁም ሀሳብ በማዋጣት ለቀጣይ የሃገራችን የብልጽግና ጉዞ መደል የሚሆን አሻራችሁን እንድታሳርፉ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት ለውይይት መነሻ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ ሲል የከተማው ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
