ngj

Spread the love

በግምገማ መድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ እንደተናገሩት ጉዳዩ የገፅታ ግንባታና የዞኑን የስፖርት ዘርፍ ለማነቃቃት በዚህም አካባቢያችንን ለዓለም አጉልቶ ለማሳየት ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ እንደ ዞን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እስከ ታችኛው ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ተሣታፊዎች በአግባቡ መለየታቸውን ተናግሯል።

የቦታ ዝግጅት፣የፓናል መወያያ አዳራሽ የማዘጋጀትና የማስዋብ ሥራ፣ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችል የመስተንግዶና የተሽከርካሪዎች ዝግጅት በስፋት የተሰሩ ሥራዎች መሆናቸዉም ተገምግሟል።

በሚዲያ ና ቅስቀሳ፣ ተማሪዎች በነቂስ ወጥቶ በዓሉን እንዲሣተፉና በተመሣሣይ መልኩ የተለያዩ የስፖርት ተቋማትም በስፍራው በመገኘት ፕሮግራሙን በልዩ ልዩ ትርዒቶች እንድያደምቁት የሚደረግ ሲሆን በዚህ ወቅት የብስክሌትና የሩጫ ውድድሮች እንደሚካሄዱም በግምገማ ወቅት ተመላክቷል።

የከተማው ማህበረተሰብ ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቁ በኩል አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለበት ጥሪ ተላልፏል።

የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ለአቀባበል ስነ-ስርዓቱ በካፋ ዞን የተደረገውን ዝግጅትና ለጉዳዩ በዞኑ በኩል በሁሉም ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረት አድንቀው በቀሪ ተግባራት ላይ ቢሮ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት የችቦ አቀባበል ስነ ስርዓቱን በጋራ ርብርብ ለማሳካት ጥረት እንደሚያደርግ አስተያየታቸውን ሰጥቷል።

መርሃ ግብሩን እንዲሳካ የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አቶ ፋንታሁን አሳስቧል።

መረሃ ግብሩ በነገዉ ዕለተ የአዳራሽ ፓናል ውይይት ከቀኑ 8 ሰዓት የሚካሄድ ሲሆን መጪዉ ቅዳሜ የአደባባይ በዓልና የችቦ አቀባበል ስነ – ስርዓት ከጧቱ 2:30 ጀምሮ በቦንጋ ከተማ መሃል አደባባይ እንደሚካሄድ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል ሲል የዘገበዉ የካፋ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *