የክልሉ መንግስት በክልሉ ያለውን እምቅ አቅምና ጸጋ ወደ ሚጨበጥ ሀብት ለመቀየር በተጨባጭ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባር በመግባት እየሰራ

Spread the love

የክልሉ መንግስት በክልሉ ያለውን እምቅ አቅምና ጸጋ ወደ ሚጨበጥ ሀብት ለመቀየር በተጨባጭ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባር በመግባት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት ምክትል አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መሰለ ከበደ ተናገሩ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የብሔረሰቦች ምክርቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተከበሩ አቶ መሰለ ከበደ ቀርቧል።

አቶ መሰለ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ክልላችን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በአይነት ፣በይዘትና በጥራት መጠነ ሰፊ እና ግዙፍ ፋይዳ ያላቸውን ጠቀሜታዎች ለህዝቡ ያጎናጸፈ ስለመሆኑም በሪፖርቱ አመላክተዋል ።

የክልሉ መንግስት ተቋርጠው ለቆዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከፍ ያለ ትኩረት በመስጠቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓልም ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በክልሉ ያለውን እምቅ አቅምና ጸጋ ወደ ሚጨበጥ ሀብት ለመቀየር በተጨባጭ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባር በመግባት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ቀን በሁሉም አካባቢዎች በተደራጀ መንገድ መከበሩንም በሪፖርቱ አመላክተዋል።

ምክርቤቱ ሰው ተኮር ተግባራትን ከመፈጸም አኳያ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአረጋውያንን ቤት በማደስ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ መወጣት መቻሉም ተብራርቷል ።

የህገመንግስትና የፌዴራሊዝም ግንዛቤ በመፍጠር የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤትና የክልሉ ምክርቤት በጥምረት በመስራት የብሔረሰቦች መብት የማስከበር ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል ።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ከመፍታት አኳያ ለብሔረሰቦች ምክርቤት አራት አቤቱታዎች ቀርበው እልባት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም አቶ መሰለ አብራርተዋል ።

የብሔረሰቦችን የጋራ እሴት ለይቶ ከመስራትና ከማጎልበት አኳያ እንዲሁም የብሔረሰቦችን እኩል የመልማት ጥያቄን ከማረጋገጥ አንጻር ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ መሰለ አብራርተዋል ።

ዘላቂ የሰላም ግንባታና የአቅም ማጎልበት ስራዎችም ተጠናክረው ስለመሠራታቸው አቶ መሰለ በሪፖርቱ አመላክተዋል ።

የክልሉ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች የመንግስት ዕቅድ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግብ በእውነትና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ብርቱ ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በአባላት አስተያየት እና ጥያቄዎች በመቅረብ ላይ ይገኛል።

በታጠቅ አበበ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *