ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የአስፈጻሚ አካላት የተግባር አፈጻጸም እየገመገመ ነው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የአምስቱም ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ወራት የአስፈጻሚ አካላት የተግባር አፈጻጸም ረፖርት በታርጫ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤና የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ጸሐይ ደርጫ በመድረኩ መክፈቻ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የአስፈጻሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም መከታተል፣መቆጣጠርና ተግባራትን መገምገምና ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮችን ማረም ዋነኛ ተልዕኮ ነው።

በዚህም የምክር ቤቱ ስራዎች በአግባቡ እየተሰሩ መሆኑን መከታተል፣የመንግስትና የህዝብ ሀብት ስራ ላይ ስለመዋሉን፣ፈጣንና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ፣ማህበራዊና ፖለቲካ ስራዎች በዕቅዱ መሠረት መከናወኑን፣የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መስፈኑን፣የዜጎች መብት፣ደህንነትና ጸጥታ ስለመከበሩን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል በንግግራቸው።

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በዓመት ሁለት ጊዜ በመንግሥት አካላት የተቀናጀ አሰራር መኖሩን ለማረጋገጥና በተግባራት ጠንካራና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመገምገም ለተቋማት ገንቢ ግብረመልስ እንደሚሰጥም ምክትል አፈ-ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የየተቋማቱ የተግባር ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርት በየዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች እየተገመገመ የሚገኝ ሲሆን በመድረኩም የአምስቱም ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የተቋማት የሥራ ሃላፊዎች እና የቢሮው ማኔጅመንት አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *