ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በኢሰራ ባሌ ከተማ አስተዳደር ከ12.3 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የኢሰራ ባሌ ከተማ ሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፍተዋል።
ይህ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንሸቲቭ የሆነው ቅድሜ ሞዴል ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራት ችግር በመፍታት፤ ስብራትን ለመጠገን በክልሉ በዘርፉ እየተከናወኑ ካሉት ዘርፌ ብዙ ተግባራት አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
በተያያዘው ዜና በክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በ53.1 ሚለየን ብር በኢሰራ ወረዳ የተገነባው የባሌ -ሾታ 12.37 ኪሜ መንገድ መርቀው ከፍተዋል።
የመንገዱ መገንባት 5 ቀበሌዎችን ከወረዳ ማዕከል የሚያገናኝ ሲሆን ከ16ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ገልጸዋል።
በጌታሁን ግርማ
የክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳና ባሌ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች መርቀው ከፍተዋል።
ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በኢሰራ ባሌ ከተማ አስተዳደር ከ12.3 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የኢሰራ ባሌ ከተማ ሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፍተዋል።
ይህ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንሸቲቭ የሆነው ቅድሜ 1ኛ ሞዴል ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራት ችግር በመፍታት፤ ስብራትን ለመጠገን በክልሉ በዘርፉ እየተከናወኑ ካሉት ዘርፌ ብዙ ተግባራት አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
በተያያዘው ዜና በክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በ53.1 ሚለየን ብር በኢሰራ ወረዳ የተገነባው የባሌ -ሾታ 12.37 ኪሜ መንገድ መርቀው ከፍተዋል።
የመንገዱ መገንባት 5 ቀበሌዎችን ከወረዳ ማዕከል የሚያገናኝ ሲሆን ከ16ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ገጸዋል።