








የሚዛን አማን ከተማ ኮርደር ወደ ስራ ከገባ ጊዜ አንስቶ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም እንደገለፁት ከተማው እንደ ሀገር በኮሪደር ልማት ስራ ከተካተቱ 30 ከተሞች አንዱ መሆኑ ገልፀዋል።
ከተማዋ እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ከተማ ከመሆን ባለፈ በሀገር ደረጃ ለቱሪዝም ምቹና ተመራጭ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
በኮርደር ልማት ስራው ከመገባቱ በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ ልምድ ለመውሰድ ተሞክሯል ያሉት ከንቲባው አጠቃላይ በሚዛን አማን ከተማ 21 ኪሎ ሜትር በዚህ ዙር ለማልማት ልየታ የተደረገባቸዉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በልየታው አዲስ ከተማ ፣ ህብረት ፤እድገትና አማን ቀበሌዎች የተካተቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የአማራጭ መንገዶች ችግር የሚስተዋል መሆኑን ገልፀው አዳዲስ አማራጭ መንገዶችንም በኮሪደር ልማት ስራው በማካተት የመንገድ ከፈታ ስራዎች እየተከናወኑ መኖራቸውንም ገልፀዋል።
በከተማው የሚስተዋለውን የመንገድ ጥበትና ፣ የመኪና መጨናነቅ ፣ የእግረኛ መንገድ ችግርና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ዘላቂ መፍትሔ መፍጠር ይገባል ብለው በዚህም የኮብልስቶን ንጣፍ ስራዎች፣ 2.1 ኪሎ ሜትር አዲስ መንገድ ከፈታና የዲች ቦይ ግንባታ ስራዎች እስካሁን መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
የኮርደር ልማት ስራው በዚህ አመት ህገወጥ ቦታዎች ነፃ በማድረግ በቀጣይ አመት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ስራ የሚገባ መሆኑንም ገልፀዋል።
የአረንጓዴ ልማት ስራውን ለማከናወን በጨረታ ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀው ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን ለመፍጠር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶም እየተሰራ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡ በኮሪደር ልማት ሰራ አሁን እያሳየ ያለውን መነሳሳት አመስግነው በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ልማቱ እንዲፋጠን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ሲል የዘገበዉ የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።
መንግስት መሰረተ ልማት ለማሟላት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡም ልማትን ሙሉ በሙሉ ለማሟላት ድጋፉን አጠናክሮ ማስቀጠል አለበትም ነው ያሉት።
