ጉባ የኢትዮጵያውያን ትግስት ፣አንድነት ና የማይበገር መንፈስ የታየበት ስፍራ ነዉ ሲል አቶ አቶ ኢብራሂም ተማም ተናገሩ

Spread the love

የጉባ ብስራቶችና የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች በሚል መሪ ቃል በገሣ ጫሬ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም የብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ሆኖ አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል።

ጉባ የኢትዮጵያውያን ትግስት ፣አንድነት ና የማይበገር መንፈስ የታየበት ስፍራ ነው በማለት ብስራቱ የጨለማ መሸነፍ እና ብርሃን መፈንጠቅ ማብሰያ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ዳር ለማድረስ ለዓለም ያሳየችበት ትልቅ መሣያ ነውም ብልዋል

በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማሣተፍ ለዘላቂ ተጠቃሚነት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

የገሣ ጫሬ ከተማ አስተዳደር አቶ ምስጋው ማርቆስ በበኩላቸው የመደመር መንግሥት እንደአገር እያከናወነ የሚገኘው የልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪና ውጤት የታየባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህን የልማት ተግባራትን አጠናከሮ በማስቀጠል የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል ሥራ ላይ በተቀናጀ ርብርብ እየተሠራ እንደሆነም አቶ ምስጋናው ገልጸዋል።

የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ የጉባ ብስራቶችና የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች በሚል የመወያያ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በመድረኩም የተለያዩ ማበራዊ መሠረት ያሉ ክፍሎች ተሳትፈዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *