









የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብ ሰርዓትና የስርዓተ–ምግብ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ከአግሪካልቸራል ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ጋር በመተባበር በ“የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን የፍኖተ ካርታ ወርክሾፕ እና ክላስተር 7 ግንዛቤ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው በክልሉ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት፣ በተቀናጀ አቀራረብ እና በክላስተሪንግ ስርዓት ለመለወጥ የሚያግዙ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ የሚያጠነጥን ነዉ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምግብ ስርዓትና ስርዓተ–ምግብ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ኃላፊ አቶ ማትዎስ ማልዳዬ በሰጡት ንግግር፣
የምግብ ስርዓት ለውጥ በክልሉ ልማትና በህብረተሰቡ ጤና ላይ ያለውን አስፈላጊነት በማብራራት የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅትና ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
አክለዉም የምግብ ስርዓት ለውጥ ፍኖተ ካርታ በክልሉ ዘርፉን በማዘመን፣ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር እና ለማሻሻል ያለውን አስፈላጊነት ለማህበረተሰቡ ማስረጥ እንሚጠበቅበት ገልጸዋል።
በተጨማሪም ባለፈው በጀት ዓመት በባለድርሻ ተቋማት የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ በማሻሻል አጠቃላይ የክልሉን የምግብ ስርዓት ለውጥ ካርታ በጋራ ላዉንች እንደሚደረግ በመግለጽ ሁሉም የስርዓተ ምግብ ፎካሎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉና ተግባራዊ እንድያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ለውጥና የአመጋገብ ሁኔታ ማሻሻል ላይ ያተኮረ የቀጣይ አቅጣጫ ስልጠና የኢትዮጵያ ከአግሪካልቸራል ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ክላስተር አንድ አስተባባሪ አቶ መሠረት ፀጋዬ ተሰጥቷል።
ተሳታፊዎች በምግብ ስርዓት ለውጥ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና በተግባር ለማጠናከር እና የተሻለ የአመጋገብ አገልግሎት ለማረጋገጥ የሚያግዙ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በግንዛቤ መስጫ መድረኩ የክልሉ ከተለያዩ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ፣ ከቴክንክና ሙያ እና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተዉጣጡ የስርዓተ ምግብ ፎካሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። መድረኩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
