




የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በኮንታ ዞን ለሚገነባው የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ና በተቋም ግንባታ ስር የሰደዱ ሰብራቶችን በመጠገንና በማከም በርካታ ስኬቶችና ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
እነዚህ ስኬቶች የህዝቡን ሁለንናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር የፓርቲያችን ቅቡልነትን ያረጋገጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጥልቅ እሳቤዎች ባለቤት የሆነው ፓርቲያችን ቃሉን አክባሪ የተግባር ፓርቲ መሆኑንም በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በተጨባጭ እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።
ሀሳብ፣ ተግባርና ውጤትን በማጣመር ስብራቶች ተጠግነው ወደ ላቀ ከፍታ የመሻገር ጽኑ መሰረት ተገንብቷል ያሉት አቶ ፍቅሬ ጠንካራ ተቋማት ግንባታ ስራዎችን በማስቀጠል አገረ መንግሥት ግንባታውን ስኬታማ ማድረግ የብልጽግና ፓርቲ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመዘርጋት የተቋም ግንባታውን ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ መጠነ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
በግንባታውም ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ የፓርቲያችን ባህልም ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፍቅሬ በኮንታ ዞን የሚገነባው G+3 የህንጻ ግንባታ ስነ ስርዓት ፓርቲያችን ብልጽግና 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶውን ባስተዋወቀበት ማግስት መሆኑ ለየት ያደረገዋል።
በዚህም የሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ መንትያ ግቦችን ለማሳካት አመራርና አባላት የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ለዘመናት ስር የሰደዱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አየነቀለ የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።
ፓርቲያችን ብልጽግና ምቹ የስራ አካባቢ ፣ የተቀላጠፈ አገልግሎትና ዘመናዊ አሰራርን ለመተግበር ከነደፋቸው የተቋም ግንባታ ስራዎቻችን አንዱ ነው ብለዋል።
