የማሻ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታን በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የማሻ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታን በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን የስራ ተቋራጩ ገልጿል።

በሾደብ ኢንጂነሪንግ የማሻ ንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ አቶ አብያለው ቅጣው እንደገለፁት የውሃ ግንባታን በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ለዚህ የአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍና ትብብር የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል።

የከተማው ውሃ ዝርጋታ 28 ኪሎሜትር የሚሸፍን መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጁ 18ኪሎሜትር ዝርጋታው የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪው 10 ኪሎሜትር የዝርጋታ ስራ ፈጥኖ እንደሚጠናቀቅም ከከተማው አስተዳደር እና ሌሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለግንባታው መፋጠን የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እያበረከቱ ያሉት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ተናግረው ድጋፍና ክትትላቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

የውሃ ሪዘርቫየር ግንባታና ሌሎች የግንባታ ስራዎች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ግንባታውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ የሚፈጅ መሆኑንም የሸካ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *