



የወባ ወረርሽኙን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ከፍተኛ ጥረት አጠቃላይ የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባምና ባለድርሻ አካላትም በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅ ተመልክቷል ።
ክረምት መግባቱን ተከትሎ የወባ ስርጭት ከፍ እያለ በመሆኑ ህብረተሰቡን በማስተባበር የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ለመስራት በየዞኖቹ የ90ቀን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንና ለዚህም ማህበረሰቡ የአካባቢውን ንጽህና በሚገባ በመጠበቅ የወባ ወረርሽኝ ከሚያመጣው የጤና እክል ራሱን ሊከላከል እንደሚገባ ተገልጿል።
በተለይ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ እና ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርጉ በተለያዩ ምክንያት የተቆፈሩ ቦታዎች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን ጉድጓዶችን ጊዜ ሳይሰጥ ማዳፈን ዋነኛ መፍትሔ መሆኑ ተጠቁሟል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
