




የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ 23ኛ የአስተዳደር ጉባኤ በተለያዩ ዝግጅት እያካሄደ ነው።
እንደ ሀገር የትምህርት ሴክተሩ ላይ የገጠመውን ስብራትን ለማከም የተለያዩ ስራዎችን በመስራት በርካታ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ በጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ገልጸዋል።
የትምህርት ዉጤታማነትን ለማሻሻል በተቀናጀ አግባብ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያሉት አቶ አልማው ዘውዴ ካፋ ዞን የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን የእውቀት መፍለቂያ አከባቢ እንደሆነም አስረድቷል።
ትምህርት ላይ መሠራት ትዉልድ ላይ መሠራት በመሆኑ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ሌሎችም ዘርፉን በመደገፍና ለዉጤቱም ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ትውልድ የሚያመሰግን መሆን አለብን እንጅ የታሪክ ተወቃሽ መሆን የለብንም ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል።
በክልል ደረጃ የዘርፉን ዉጤታማነት ለማሳደግ በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ነዉ ያሉት አቶ አልማዉ ዘዉዴ፣ ከዚህም ዉስጥ የትህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና ግብዓቶችን ማሟላት ይገኝበታል ብለዋል።
የካፋ ዞን በትምህርት ለትዉልድ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡንና ሌሎች አካላትን በማስተባበር እየሰራ ያለዉ ስራ ዉጤት እያመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስቧል።
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ መድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ትውልድ መልካም ስነ-ምግባር በዕውቀት የታነጹ እንድሆኑ ትምህርት ላይ መስራት ምንም መተኪያ የሌለ ነው ብለዋል።
የትምርህት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ግብዓት ለማሟላት በዞን መንግስት በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው አሁንም ከሁለም አካላት ትኩረት ሰጥተው መስራትን ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል።
ሀገር ለመገንባት የተማረ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት አቶ እንዳሻው ከበደ በዞናችን የትምህርት ቤቶችን ላይ ግብዓት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን ተናግረው የመንግስት እጅ ያጠረበት አከባቢ ህብረተሰብን፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማስተባበር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዞናችን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከዞን አስተዳደር ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ ተናግረዋል ።
በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ አቅም የተፈጠረው ሀገራት በትምህርቱ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የተለያየ እንደሆነ በመግለጽ የትምህርት ጥራት ጉዳይ አሁን ጥያቄ ምልክት ውስጥ በመሆኑ አሁንም አጽንኦት ሰጥተው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በሀገራችን የተጀመረውን የትምህርት ፖሊስ ላይ የተደረገውን ማሻሻያ በዞናችን ወደ ስራ በማስገባት ውጤት እያስመዘገብን ነው ፤ከኩረጃ የፀዳ ትውልድ መፍጠር፣ ትምህርት ለትውልድ ላይ ህብረተሰቡን በማስተባበር የትምህርት ግብዓት ማሟላትና ሌሎች ነገሮች ለአብነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
