



ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ በግብርና መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ፣የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ፣የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል።
በስልጠናው መርሃ ግብር የክልሉ ቡና ሻይና ቅመማቅመም ባለሥልን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኮጁአብ እንዳሉት በአመራሩና በአባላት መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው የአባላትን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም ከመገንባት ባሻገር የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በዛሬው የስልጠና መርሃ ግብር የክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ታመነ በቀለ በግብርና ኢንዱስትሪ ልማት ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ዘርፍ መረጃ ያመለክታል።
