




በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት ለብልፅግናችን በሚል መሪ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ሊታረስ የሚችሉ ሰፊ መሬቶችን በመለየት የማሳ ሽፋን ስራዎችን ማሳደግ እንደሚገባ በመድረኩ የተገኙት የካፋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ኃይሌ ተናግረዋል።
ወቅታዊ የግብርና ስራዎች እንዲሳኩ አመራሩና ባለሙያው ለአርሶ አደሩ የሚያደርገውን ሙያዊ ዕገዛ የበለጠ ማጎልበት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ወረዳው ከምታወቀው የግብርና ተግባራት አንዱ ከሆነው የቡና ስራ በተጨማሪ በሁሉም መስክ ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ልሰራባቸው ይገባል ሲሉ አብራርተዋል።
በቀጣይም በየደረጃው የሚገኙ አመራር እና አባሉ በቁርጠኝነት በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን በመገንዘብ ለተጨባጭ ውጤት ሊተጉ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።
የግብርና ስራዎችን ከወቅታዊ ተግባራት ከሆኑ ማዕጤመ እና የኮሪደር ስራዎች ጋር በማስተሳሰር ለውጤታማነቱ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ አቶ አጥናፉ አሳስበዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አለሙ ከስኩ በበኩላቸው የግብርና ልማት ስራዎች ላይ ቴክኖሎጂን በሙሉ ፓኬጅ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠውም እንደሚገባም አቶ አለሙ አብራርተዋል።
በወረዳው በሚለሙ ዋና ዋና ሰብሎች ላይ በሄክታር የሚገኘውን ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባህል ማድረግ ዋነኛ ተግባራችን ሊሆን ይገባልም ሲሉ አቶ አለሙ ተናግረዋል፡፡
መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የገዋታ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አርጋው ሀይሌ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ርብርብ ውስጥ የግብርና ባለሙያዎች የአንበሳውን ድርሻ ልወጡ ይገባቸዋል ብለዋል።
ወረዳው ካለው እምቅ አቅም አንፃር በግብርና ዘርፍ በርካታ ተግባራቶችን በግንባር ቀደምነት ለማሳካት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም በንግግራቸው አብራርተዋል።
በዚሁ የንቅናቄ መድረክ የበልግ የእስካሁኑ አፈጻጸም እና ሌሎች የቀጣይ ተግባራት ዙሪያ በወረዳው ግብርና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ መለሠ መንገሻ በኩል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ የዞንና የክልል ከፈተኛ አመራሮችን ጨምሮ የወረዳ አስተባባሪ አካላት እና አመራሮች፣የግብርና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆኖዋል።
