



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከዘርፉ አመራሮች ጋር አካሂዷል።
በመድረኩ ባለፉት ወራት በፓርቲው የእሳቤዎች ቅኝት የተከናወኑት ተግባራት የነበሩ ጥንካሬዎች የተፈተሹበት ፣እጥረቶችን ነቅሶ በመለየት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።
በፓርቲው እሳቤዎችና መርህ ላይ የተቃኘ ለሁለንተናዊ የብልፅግናን ጉዞ ስኬት መሰረት የሚጥሉ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።
በዚህም ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስትና ጠንካራ ሀገር የመገንባት ተልዕኮውን ለመወጣት በፓርቲው መሪነት እየተከናወነ ያለው ተግባር አበረታች ናቸው።
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በግምገማው መድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ ባላፋት ወራት በፓርቲው እሳቤዎች የተመዘገቡት ስኬቶች ተስፋ ሰጭና ለብልጽግና ጉዞ ስኬት መሠረት የሚጥል ሲሆን ክልሉ ካለው እምቅ አቅም አንጻር የዕቅድ ክለሳ በማድረግ ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።
በመፍጠንና በመፍጠር እሳቤዎች በየአካባቢው ያሉትን ሀብትና ፀጋዎችን በማጤን፣በመለየትና አስተውሎ በማልማት ለህዝቡ ተጠቃሚነት መረባረብ ጊዜው ይጠይቃል ብለዋል።
የፓርቲያችን እሳቤዎች ፣ወንድማማችነት፣አህትማማችነትና አብሮነት በማጎልበት ሀገራዊና ክልላዊ ሀብቶችን አቀናጂቶና አስተባብሮ በማልማት ለብልጽግና ጉዞ ስኬት ማዋል ይኖርብናል ነው ያሉት።
የፓርቲያችን ኢኒሼቲቮች የሆኑት የበጋ መስኖ ስንዴ፣የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣የበጎፍቃድ አገልግሎትና ሌሎች መሠል ተግባራትን በተደረጃና በተቀናጀ ሁኔታ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የፓርቲ ተቋማት የአመራርና የአባላት መረጃ አያያዝ እንዲዘምንና ወቅቱ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እንዲመራ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ማጠናከርና የመረጃ ማስተዳደር ብቃትን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ መስራት ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።
የፋይናንስ ስርዓት ወጭ ቆጣቢ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ግልጽና ለተጠያቂነት የተመቸ እንዲሆን ማድረግ በቀጣይነት በውጤታማነት መሰራት ይጠበቃል ብለዋል።
የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍትሔ አካል በመሆን ተግባራት በትግል መምራት ይጠበቃል ያሉት አቶ ፍቅሬ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ባህል እስኪሆኑ ድረስ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
በፓርቲው እሳቤዎች እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ተስፋ ሰጭና ለብልጽግና ጉዞ ስኬት መሠረት የሚጥሉ መሆኑን የገለጹት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ናቸው።
አዎንታዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ፣ ከተረጂነትና ልመና አስተሳሰብ መላቀቅ፣ የመልካም አስተዳደር ስራዎችና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ ልዩ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ እንደገለጹት በፖለቲካ አቅም ለመገንባት እየተሰጠ ያለው ስልጠና በአመራሩ ፣በአባሉና በህዝቡ ዘንድ የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለማጎልበት ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደተቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ህዝቡ ግንባር ቀደም በመሆን በተለያዩ መሠረተ ልማት ስራዎች ላይ ሊነገር ና ሊጠቀስ የሚችል አብነታዊ ማሳያዎችን ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል።
