




የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትላንትናው ምሽት ለተበረከተላቸው ‘የኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ኒሻን’ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ እና ሀብታም ስልጣኔዎች አንዱ በሆነ ሀገር መከበር፤ እጅግ በጣም ኩራት የሚንጸባረቅበት ነው ብለዋል።
ይህ ክብር ባለፉት ዓመታት አጋርነታችንን ለቀረጹ እና ላጠናከሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህንዳውያን ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ህንድ ተቀያያሪ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ ሆና እንደምትቀጥልም አስታውቀዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
