1445ኛው የረመዳን ወር ፆም ነገ ይጀመራል

Spread the love

1445ኛው የረመዳን ወር ፆም ነገ ሰኞ መጋቢት 2 እንደሚጀመር የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተተከሉ አስራ አንድ አስትሮኖሚ ማዕከሎችን መሰረት በማድረግ ባሰባሰበው መረጃ ጨረቃ መታየቷ አሳውቋል።

ይህንን ተከትሎም የረመዳን ፆም ነገ ሰኞ እንደሚጀመር ይፋ አድርጓል።

ታላቁን የረመዳን ወር በመተሳሰብና አላህን በመለመን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መግለጻቸው ይታወሳል።

የምንቀበለው የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልንም ብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *