



የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን በቦንጋ ከተማ 180 ሺህ በሚሆን የገንዘብ ወጪ የሚሰራ የአቅም ደካሞች ቤት ግንባታ ስራ አስጀምሯል፡፡
ቤት ግንባታ ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የ2016 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ከነዚህም በጎ ተግባራት መካከል አንዱ የአቅመ ደካሞችና የድሃ ድሃ ወገኖች ቤት ግንብቶ መስጠት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ነወ አቶ አልማው የተናገሩት።
ለዚህም የክልሉ መንግሥት በሁሉም ተቋማት የሚገኙ ቢሮዎች አንድ አንድ ቤት በግላቸው ገንብተው ለአቅመ ደካሞችና የድሃ ድሃ ወገኖች ገንብተው እንዲያስረክቡ አቅጣጫ በተቀመጠው መሠረት ዛሬ በቦንጋ ከተማ ላይ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መነጅመንትና ተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን የአንድ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ማካሄዱን ገልፀዋል ፡፡
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በክረምት የአቅም ደካሞች ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በክልሉ ከሚከናወኑ ሰው ተኮር አገልግሎት አንዱ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው አቶ አልማው ዘውዴ የገለጹት ፡፡
ብልጽግና ፓርት ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉት አቶ አልማው አቅመ ደካሞችና የድሃ ድሃ ወገኖችን በተለያዩ አጋጣሚዎች መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አቅም በፈቃደ መጠን መድረስ የሚችልና አንዱ ለአንዱ መድረስ የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር ነውም ብለዋል፡፡
አቶ አልማው ዘውዴ አክለውም በሀገራችንና በክልላችን በጎ ፍቃደኞች ደም በመለስና የተለያዩ በጎ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን በመንግሥት በጀት ልሸፈን የማይችል በርካታ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት በማዋጣት የህዝብ አቅም በተደራጀ መንገድ አንዱ አካል በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑ ይህንን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ሠራተኞች እና የቢሮው አመራሮች የአንድ አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ በቦንጋ ከተማ ዛሬ ማስጀመራቸው ጠቁመው ይህ በጎ ተግባር በትምህርት ቢሮ ብቻ የሚቆም ሳይሆን በቀጣይ በትምህርት ኮሌጆች እንዲሁም በየደረጃው ባለው ትምህርት መምሪያዎች አቅም በፈቃደ መጠን እየተቀናጀን የተለያዩ አካላትን እያስተባባረን በዚህ ክረምት በርካታ የድሃ ድሃ ቤቶችን የመጠገን ስራዎች እንደሚሰሩም አቶ አልማው አንስተዋል ።
የቤቱ ግንባታ አጠቃላይ 180 ሺህ በሚሆን የገንዘብ ወጪ የሚሰራ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
