የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ለሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።

Spread the love

ለሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱን ያስጀመሩት የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ በክልሉ ሁሉም ዞኖች የቅድመ ጉባዔ ስራዎች ተጠናክረው በየደረጃው ይቀጥላሉ ብለዋል።

‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ በፓርቲው አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ በሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ከአመራር እስከ አባላት የተጠናከረ ውይይት እንደሚደረግም አቶ ነጋ አበራ ተናግረዋል ፡፡

በውይይቱም በአንደኛው ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸሞች፣ በፓርቲው ስነ ምግባር የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ በተሰሩ ስራዎች እና በፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ ላይ በሚኖሩ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ አመራሩ ውይይት እንደሚያደርጉ አቶ ነጋ አስገንዝበዋል ።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ባቀረቡት ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደበት ነው።

አቶ ማስረሻ በላቸው ባቀረቡት “ከቃል ወደ ባህል “በየደረጃው ለሚገኘው አመራርና አባላት ለውይይት መነሻ በሚሆን ሰነድ ላይ ማብራሪ ሰጥተዋል።

ከዚህ በፊት በሀገራችን የተተገበሩ ለውጦች በአዲስ ሀሳብ ያልተደገፉና ዘላቂ የባህል ሽግግር ማምጣት ያልቻሉ እንደሆነ የገለጹት አቶ መስረሻ መደመር አዲስ ዘመንና የባህል ሽግግር የሚያመጣ አሻጋሪ ሀሳብ ነው፡፡

መደመር የሀገራችን ሁለንተናዊ ስብራትና ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን በተሟላ መልኩ ለመመለስ የሚረዳ አዲስ እሳቤ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅድመ ጉባኤው ውይይት ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉበት እንደሚገኙም ታውቋል ፡፡

የቅድመ ጉባኤ ውይይቶችና የአባላት ኮንፍረንስ እስከ ጉባኤው መዳረሻ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *