የቡና ምርታማነትና ጥራት በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘዉን የዉጭ ምንዛሬ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን። ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቡና ምርታማነትና ጥራት ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ይገኛል

በንቅናቄው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልሉ ከፍተኛ ቡና የማምረት አቅም ያለዉ መሆኑን ጠቅሰዉ በምርታማነትና በጥራት ላይ በመስራት የህብረተሰቡንም ሆነ የሀገርቱን ከኢኮኖሚ ከማሳደግም ባሻገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያመጣ እንደሆነ አንስተዋል ።

ለዚህም መንግስት የተለያዩ በዘርፉ የተለያዩ የፖሊስ ማሻሻያ እና የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻሉና ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ዋነኛ ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ይሁን እንጂ ለም አፈር፣ ምቹ የአየር ፀባይ ያለው ክልል ባለን ዕምቅ አቅም ልክ ከማምረት ብሎም ምርታማነትንና ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር ገና ስራ እንደሚፈልግ አሳስበዋል ።

ለዚሁም የተደራጁ ዩኒየኖች እና ማህበራት ትልቅ ሚና እንዳላቸው በማስታወስ በቀጣይ ክልላችን 67ሺ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ያቀደችውን ለማሳካት የባለድሻ አካላት በምርታማነትና ጥራት ላይ በቅንጅት መስራት፣ የግብይት ማነቆውን መፍታት እንደሚገባ በአጽንኦት አንስተዋል ።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ኢፌዴሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ መንግስት የዘርፉን ምርታማነትና ጥራት በማሳደግ ዘርፉ የሚያመነጨውን ገቢ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን ገልጸዉ ለዚሁም በምርታማነትና በጥራት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት ለመስራት ይህንን የንቅናቄ መድረክ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉ ዞኑ የቡና ምርትን በሚመለከት ከ2009 እስከ 2016 ዓ/ም ድረስ 178 ሺ ቶን ምርት ለገበያ ያቀረበ መሆኑን ገልጸዉ በቀጣይ በምርታማነትና ጥራት ላይ ትኩረት እንደሚሻ ገልጸዋል ።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የኢፌዴሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ፣ የፌደራልና የክልል አመራሮች፣ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎችና የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ በቡና ልማትና ግብይት ላይ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች እንዲሁም ሌሎች የባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *