የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል አለ፡፡

የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንዳሉት፤ መንግስት የኑሮ ውድነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን የኢኮኖሚ ሁኔታ በማጤን የሠጠው ምላሽ ይደነቃል።
መንግስት ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ በቋሚ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች አንፃራዊ እፎይታ ይሰጣል፡፡
ማሻሻያው በአነስተኛ ደመወዝ እየሰሩ ያሉ ተቀጣሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡
መንግስት ደመወዝ ከማሻሻል ባለፈ የመንግስት ሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል 6 ሺህ ብር እንዲሆን መወሰኑ ለዘመናት በሰራተኛው እና በኮንፌዴራሽኑ ሲጠየቅ የነበረ ጥያቄ ፍሬያማ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የደመወዝ ማሻሻያው ለታለመለት ዓላማ መዋል እንዲችል በየደረጃው የንግድ ስርዓቱ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት የሠራተኞችን ደመወዝ በማሻሻል ያሳየውን ቁርጠኝነት የግል ድርጅቶችም ሊከተሉት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
በጭማሪው የተካተተውን ዝቅተኛ የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ ወለል እንደ ተሞክሮ በመውሰድ በጅምር ላይ ያለውን የሠራተኛ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የመወሰን ስራ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲደረግ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
